አበባ ናት ቆንጆ / ቀለም ያለው/
(የዓለሜ ቤት አፃፃፍ)
እምቡጧ ስትፈነዳ ፈክታ አያታለሁ፣…………..7/7
አበባዋን ወድጄያት ውበት አደንቃለሁ፡፡……………..7/7
የቀለሟ ምርጫዬን ማወቅ ቢከብደኝም፣…….7/6
ግን የርሷ አፈጣጠር ቀልቤን ማረከኝም፡፡……….7/6
መማግ ነው ሽታዋን ቀንጥሼ የፈካችውን፣………6/7
ከአየር በመሳብ ጣፋጭዋ መዓዛዋን፡፡…….6/7
ከውቦቹ መሃል ድናግል ሆና ወድጄያት፣………..6/7
ከአበቦች ለይቼ በፍቅር ሳሎን ማኖራት ፣……….6/7
ፍሬዋን ተከልኩና እንድታድግ አደረግኳት፡፡………..6/7
ዙሪያዬን ቢሞላም የምርጦቹ ፍሬ፣………..7/5
አበባዬ ቆንጂቷ ውበት ሚስጥሬ፡፡…………….7/5
ልብሷ ነው ቅጠሏ በቀለም ተነክሮ፣………6/6
በብሩሽም ሳትቀባ አምራ በተፈጥሮ፡፡……..6/6
አማላዬ ልትሆን ለእኔ ስጦታ፣………..6/4
በምድር የበቀለች ናትና እይታ፡፡……….6/4
ሀሴትን ማደርግባት በቁንጅናዋ እንድረካ፣……….7/6
የምስማት የማሸታት በከንፈር የምትነካ፣……………7/6
አበባዬ ናት ፍቅሬ ከሁሉም ሰልካካ፡፡………7/6
Alemseged Sisay W., Addis Abeba, Ethiopia.
This poem has not been translated into any other language yet.
I would like to translate this poem